Phillipine Mtikitiki በደቡብ አፍሪካ ለሚገኘው የአሜሪካ ንግድ ማህበራት ፕሬዘዳንት ሆነው ተመረጡ።
በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የአሜሪካ የንግድ ምክር ቤት (AmCham) የደቡብ አፍሪካ ኮካ ኮላ ፍራንቻይዝ ምክትል ፕሬዝዳንት Phillipine Mtikitiki ን የፕሬዚዳንትነቱን ሚና እንዲወስዱ መርጧል። የጄነራል ኤሌክትሪክ ስራ አስኪያጅ የነበሩት Lee Dawes ን ተክተው ይሰራሉ።
03-11-2022
ከዚህ ቀደም Phillipine የ AmCham ተባባሪ ምክትል ፕሬዚዳንትነትን ሚና በመያዝ ስታገለግል ቆይታ ነበር። የቀድሞው ፕሬዚዳንት Lee Dawes እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፣ "የአሜሪካ ንግድ ምክር ቤት Phillipine ን ከታላቅ ደስታ ጋር እንኳን ወደ ፕሬዚዳንትነት ኃላፊነት በደህና መጣሽ ይላታል። ድርጅቱ ወደፊት እንዲጓዝ ከፍተኛ አስተዋጾ እንደምታበረክት ምንም ጥርጥር የለንም።"
Phillipine በምፑማላንጋ ግዛት ተወልዳ የኢኮኖሚክስ ዲግሪዋን ከክዋዙሉ-ናታል ዩኒቨርሲቲ አግኝታለች፤ በተጨማሪም የማስተርስ ዲግሪዋን ከሪዲንግ ዩንቨርሲቲ ሄንሊ ቢዝነስ ክፍል አግኝታለች። በ 2019 እ.ኤ.አ የምስራቅ እና ማእከላዊ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት እና ዋና ስራ አስኪያጅ ሆና እንድታገለግል ተሹማ ነበር። በዚህ ጊዜ የኮካ ኮላን ስርዓት በ 12 አገሮች እንድታስተዳድር ኃላፊነት ተሰጥቷት ነበር። ዋነኛ ስራዎችዋም ንግድን ማሳደግ፣ የሰው ሀብት አቅም ማጎልበት እና ለቀጣይ ዘላቂ ዓላማ የሚውል አጋርነትን መፍጠር ነበር። በምስራቅ እና ማእከላዊ አፍሪካ በቆየችባቸው ጊዜም በኬንያ የሚገኘው የአሜሪካ ንግድ ማህበራት ምክር ቤት (AmCham) ፕሬዚዳንት ሆና አገልግላለች።
ለአፍሪካ ሴት ህጻናት ሁለንተናዊ እድገት ተቆርቋሪ ነች። ሴቶች እና ወጣቶች አቅማቸው እንዲዳብር እና የስራ እድላቸው እንዲሰፋ አያሌ ስራዎችን ሰርታለች። የእርስዋ መሾም ኮካ ኮላ ለአካታችነት እና ብዝሃዊነት ያለውን ጽኑ እምነት የሚያሳይ ነው። ኮካ ኮላ የደንበኞቹን ብዝሃዊነት ለማንጸባረቅ በ 2030 በዓለም አቀፍ ደረጃ 50 በመቶ በሴቶች እንዲመራ እቅድ ተይዟል። የ Phillipine ሹመት የዚህ ዓላማ ተምሳሌት ነው።
በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የአሜሪካ ንግድ ማህበራት ምክር ቤት በግለሰብ ከሚተዳደሩ ድርጅቶች ጀምሮ እስክ ትላልቅ ቢዝነሶች እና ተቋም አባላትን ያቀፈ ነው። በደቡብ አፍሪካ የስራ እድል ፈጠራ እና የኢንቨስትመንት ምህዳር እድገት ላይ በጋር ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ። በ AmCham አማካኝነት በደቡብ አፍሪካ እና በአፍሪካ አህጉር የምክር ቤቱ አባላት ለእድገት እንዲሁም የቢዝነስ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የጋራ የሆነ ስርዐት እና ጠንካራ ድምጽ አላቸዉ። በተጨማሪም ምክር ቤቱ የንግድ ትስስር፣ የቢዝነስ እና የትምህርት ሴሚናሮችን፣ መንግስታዊ ድጋፎችን እንዲሁም የግብይት እና የማስታወቂያ አገልግሎቶችን የመሳሰሉ ጥቅማጥቅሞች እና አገልግሎቶችን ይሰጣል።
ለኮካ ኮላ ደቡብ አፍሪካ ይህ ታላቅ ኩራት ነው። በዚህ አጋጣሚም ፊሊፒን እንኳን ደስ ያለሽ በማለት በዚህ በተከበረ ኃላፊነት ቦታ እንዲሳካላት ይመኛል።