በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች | ኮካ ኮላ ደቡብ አፍሪካ

ልየታውን ተግባራዊ ለማድረግ ምድብ ይምረጡ 

የኮካ ኮላ ዜሮ ስኳር ጣዕም ይበልጥ እንደ መጀመሪያው ኮካ ኮላ (ኮካ ኮላ ክላሲክ) እና ያለ ስኳር ጣዕም እንዲኖረው የሚያደርግ አዲስ አሰራር።

ኮካ ኮላ ዜሮ ስኳር ተብሎ አዲስ ስም የተሰጠው መጠጡ ከስኳር ነጻ መሆኑን ለማሳወቅ ነው።

አዲስ መልክ - አዲሱ እሽግ ዓለም አቀፍ አንድ ምርት እቅዳችንን ያገናዘበ ነው፤ የኮካ ኮላ ዝናን በማሳደግ ከቀይ ክብ አርማ ወደ ከስኳር ነጻ መሄዳችንን ማሳያ ነው። ኮካ ኮላ ኦሪጅናልን ይመስላል።

በጠርሙስም ይሁን በጣሳ ኮካ ኮላ ጣዕሙ ተመሳሳይ ነው። አሰራሩ አንድ ዓይነት ነው፣ ግብዐቱም አንድ ዓይነት ነው፣ የምርት ሂደቱም ሁሉ ግዜ አንድ ዓይነት ነው።

ይህን ያውቁ ኖረዋል? ጣዕምን የምንረዳበት መንገድ ብዙ ተጽኖዎች አሉት፣ ለምሳሌ፦ ኮካ ኮላዉ ምን ያክል ቀዝቃዛ ነዉ ወይም የምንጠጣበት መንገድ በጠርሙስ ወይም በብርጭቆ ቀድተን ነዉ?

በ 330 ሚሊ ሊትር ጣሳ ኮካ ኮላ ውስጥ 33 ሚሊ ግራም ይገኛል። በአንድ ጣሳ ኮካ ኮላ ውስጥ ያለው የካፊን መጠን ተመሳሳይ መጠን ካለዉ ቡና ውስጥ ካለው እጅግ እንደሚያንስ ሲረዱ ሰዎች ብዙ ጊዜ ይደነቃሉ።

በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በየቀኑ እንደ ቡና፣ ሻይ እና ለስላሳ ያሉ ካፊን ያለባቸዉን መጠጦችን ይጠቀማሉ። ካፊን ለክፍለዘመናት ሰዎች ሲወስዱት ኖረዋል። ስለዚህም ስለካፊን ብዙ ማወቅ ችለናል። በመጠጦቻችን ውስጥ በመጠኑ መጠቀማችን ጉዳት እንደሌለው ብዙ ጥናቶችም ተደርገውበታል።

ሁሉም ሰዉ ካፊን ላይወስድ ይችላል እንዲሁም ሁሉም ሰዉ ሁልጊዜ መውሰድ ላይፈልግ ይችላል። ለዚህም ነው ሰዎች ለራሳቸው እና ለቤተሰቦቻቸው አማራጭ አግኝተው መጠቀም እንዲችሉ እንደ "TAB" የመሳሰሉ ከካፊን ነጻ የሆኑ የመጠጥ አማራጮችን የምናቀርበው።

ከተፈጥሮ ምንጮች የተገኘ እና ከስኳር ነጻ የሆነ ማጣፈጫ ነው።

የስቴቪያ ቅጠሎች ለየት ያለ እና ተፈጥሮአዊ ጥፍጥና አላቸው። ከካሎሪ ነጻ ናቸው። ተክሉ የክራይሳንቴመም ዝርያ ነው። በስፕራይት፣ በግላኩ ቫይታሚን ውሃ እና ኮካ ኮላ ላይፍ መጠጦች ውስጥ ከስታቪያ ተክል በመውሰድ የስኳር እና ካሎሪ መጠናቸውን እንቀንሳለን።

ይህን ያውቁ ኖረዋል? ስታቪያን በደቡብ አሜሪካ መጠጦችን ለማጣፈጥ ከ 200 ዓመታት በላይ ጥቅም ላይ ሲዉል ነበር።

ዝቅተኛ ካሎሪ መጠን ያለው ማጣፈጫ ነው።

አስፓርታሜን ከአሴሱልፋም-ኬ ከተባለ ዝቅተኛ ካሎሪ ማጣፈጫ ጋር በማዋሃድ የተወሰኑ ምርቶቻችን ላይ ጣፋጭ ጣዕምን እንዲኖራቸዉ እናደርጋለን።

ይህን ያውቁ ኖረዋል? አስፓርታሜ ከስኳር በ 200 እጥፍ ይጣፍጣል።

የለውም።

ግብዓቶቻችን እና የምርት ሂደቶቻችን ከ 200 በላይ አገራት ላይ ባሉ መንግስታት እና የጤና ባለስልጣናት ጥብቅ ክትትል ይደረግባቸዋል። ሁሉም በተከታታይ ኮካ ኮላ ከአልኮል ነጻ የሆነ መጠጥ እንደሆነ እውቅና ሰጥተዋል። 

ይህን ያውቁ ኖረዋል? ኮካ ኮላ በዓለማችን ካሉት ከአልኮል ነጻ መጠጥ ኩባንያዎች ውስጥ ግዙፉ ነው።

የስኳር ህመምተኞች ኮካ ኮላ ላይት/ዜሮን መጠጣት ይችላሉ። ነገር ግን ስለ ስኳር ህመም እና የአመጋገብ ስርዓትን በተመለከተ ከሀኪምዎ ጋር እንዲማከሩ እንመክርዎታለን።

ካፊን በመጠኑ ያነቃቃል እና በተከታታይ ወስደዉት በድንገት ቢያቆሙ አነስተኛ የሆነ እራስምታት እና ሌሎችም አነስተኛ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሊያስተናግዱ ይችላሉ። ግን አብዛኛዎቻችን ያለምንም ከባድ ችግር ካፊንን መቀነስ ወይም ማስወገድ እንችላለን።

በዓለም ላይ ብዙ ሰዎች በየቀኑ ካፊን ያለበትን መጠጥ እንደ ቡና፣ ሻይ እና ለስላሳ መጠጦች ባሉት ዉስጥ ይጠቀማሉ። ሰዎች በኮካ ኮላ ውስጥ ያለው የካፊን መጠን በተመሳሳይ የቡና መጠን ውስጥ ካለው እጅግ እንደሚያንስ ሲረዱ ብዙ ጊዜ ይደነቃሉ።

ሁሉም ሰው ካፊን ላይወስድ እንደሚችል እናውቃለን። ሁሉም ሰው በየጊዜው መወሰድ እንደማይፈልግም እናውቃለን። ሰዎች ለራሳቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ምርጫ እንዲኖራቸው የተለያዩ ከካፊን ነጻ መጠጦችም እናቀርባለን።

ይህን ያውቁ ኖረዋል? ከካፊን ነጻ ዳይት ኮክ፣ ስፕራይት፣ ሊልት እና ፋንታን የመሳሰሉ ከካፊን ነጻ የሆኑ ለስላሳ መጠጦችን እናቀርባለን።

አዎ! የምግብ ደረጃዎች ኤጀንሲ እርጉዝ ሴቶ በቀን ከ200 ሚሊ ግራም በላይ ካፊን መውሰድ የለባትም ብሎ ይመክራል። አንድ የኮካ ኮላ ጣሳ 32 ሚሊ ግራም ካፊን ይይዛል እና አንድ የምግብ ኮክ ጣሳ ደግሞ 42 ሚሊ ግራም ካፊን ይይዛል።

ይህን ያውቁ ኖረዋል? እንደ ከካፊን ነጻ ዳይት ኮክ፣ ኦሲስ፣ ፋንታ፣ ሊልት፣ ስፕራይት እና 5 አሊቭ እንዲሁም ግላኩ ስማርትዋተርን የመሳሰሉ ከካፊን ነጻ የሆኑ ለስላሳ መጠጦችን እናቀርባለን።

አሁንም ጥያቄ አልዎት?