መረጃን ተደራሽ የማድረግ ህግ አንቀጽ 51 ን በመንተራስ የተዘጋጀ መመሪያ 2/2000 (PAIA)

የግላዊ መረጃ አዋጅ 4/2013 በተሻሻለው መሰረት

(“POPIA”)

የኮካ ኮላ ፕሮፕራይቴሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ

(የምዝገባ ቁጥር፦ 1986/003669/07)

("CCA")

የተዘጋጀበት ቀን፦ 22 ጁን 2021

1. ለ PAIA መግቢያ 1.1.  ከ 27 ኤፕሪል 1994 በፊት የደቡብ አፍሪካ መንግስት ህዝባዊ ተቋማት እና የግል ተቋማት ምስጢራዊና ቆሞ የመቅረት ባህሪ ያሳዩ ነበር። ይህም ስልጣንን ያላግባብ ለመጠቀም እና ለሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዳርጓል።
1.2.  በ PAIA  ህጎች መሰረት መረጃን ለመጠየቅ ወይም ምስጢራዊነቱን ለማረጋገጥ በፈለጉ ጊዜ PAIA ከሁሉም ተያያዥ ህግጋቶች ጋር በመሆን ከግል እና ህዝባዊ ተቋማት መረጃን የማግኘት መብትዎን ያረጋግጣል።

1.3.  PAIA  ወይም ሌሎች ህጎች የሚከለክሉ ካልሆነ በቀር ከህዝባዊ ወይም ግላዊ ተቋማት መረጃን በጠየቁ ጊዜ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

1.4.  ለዚህ መመሪያ ያመች ዘንድ፣ እራሳችንን "CCA"፣ "እኛ ወይም "የእኛ" ብለን እንጠራለን።

1.5  ይህንን መመሪያ ያዘጋጀነው የ PAIA  ጥያቄ በሚነሳበት ጊዜ ለእርስዎ ሂደቶቹን እና ሌሎች አስፈላጊ መስፈርቶችን በተመለከተ መረጃ ለመስጠት እና ለማገዝ ነው።

2.  ስለ ድርጅታችን
"CCA" ሙሉ በሙሉ በኮካ ኮላ ኩባንያ (“TCCC”) ስር የሚተዳደር፣ ሙሉ በሙሉ የመጠጥ ፋብሪካ የሆነ እንዲሁም ወደ 200 የሚጠጉ ምርቶችን የያዘ ድርጅት ነው።  ስለእኛ እንዲሁም ስለምንሰራቸው ስራዎች የበለጠ ማወቅ ከፈለጉ፣ የኩባንያችንን መረጃ https://www.coca-cola.co.za. ላይ ያገኛሉ።
3. አድራሻችን[1]
PAIA አድራሻዎቻችንን እንድናሳውቃችሁ ያስገድደናል።  አድራሻችንን ከዚህ በታች አስቀምጠናል።

የተቋሙ ስም

ኮካ ኮላ አፍሪካ ፕሮፕራይቶሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ

የተቋሙ ኃላፊ

Phillipine Mtikitiki

የኢሜይል አድራሻ

dpoafrica@coca-cola.com

የፖስታ አድራሻ

ፖ.ሳ. ቁጥር 9999

መንገድ

አድራሻ

Building 1, Oxford & Glenhove Road, Houghton Estate, 2198, Johannesburg

ስልክ ቁጥር

0860112526


4.  የ PAIA ጥያቄን ለማስገባት የት እገዛ ማግኘት ይችላሉ[2]
4.1.  የ PAIA  ጥያቄን ማስገባት ለሰለጠኑ ጠበቃዎችም ጭምር አድካሚ ሊሆን ይችላል።  ለ PAIA ጥያቄ ሂደት አዲስ የሆኑንትን ለማገዝ፣ የደቡብ አፍሪካ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (“SAHRC”) የ PAIA (“መመሪያው”) መብቶቻቸውን እንዲያስከብሩ የሚረዳዎትን መረጃ የያዘ መመሪያ አዘጋጅቷል።  መመሪያው እውቅና በተሰጣቸው ሁሉም የደቡብ አፍሪካ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ይገኛል። ለህዝብ ምርመራም ዝግጁ ሆኖ በሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ቢሮ Braampark Forum 3, 33 Hoofd Street, Braamfontein፣ ስልክ ቁጥር፦ 011 877 3600 ወይም በዚህ ድረ ገጽ www.sahrc.org.za ላይ ይገኛል።
4.2.  በ PAIA ውስጥ በተደረገው የ POPIA ማሻሻያ፣ የደቡብ አፍሪካ መረጃ ቁጥጥር ባለስልጣን ተመሳሳይ ማሻሻያዎችን በማድረግ አሁን ያለውን ተመሳሳይ መረጃ የሚይዝ በ SAHRC የተዘጋጀውን መመሪያ የ POPIA እና PAIA ማንኛውም መብቱን ለሚጠይቅ ሰው ተደራሽ ማድረግ ይኖርበታል።  የተሻሻለው መመሪያ ለህዝብ ምርመራም በመረጃ ቁጥጥር ባለስልጣን JD House, 27 Stiemens Street, Braamfontein, Johannesburg, 2001፣ ስልክ ቁጥር፦ 010 023 5200፣ የኢሜይል አድራሻ inforeg@justic.gov.za ላይ ይገኛል።

4.3.  PAIA በግል እንዲሁም በህዝባዊ ተቋማት የመረጃ ባለሙያ እንዲቀጠር ያዛል።  ኃላፊነቱ ለሌላ ሰው እስካልተላለፈ ድረስ የግል ድርጅቱ ስራ አስኪያጅ የመረጃ ባለሙያ ሆኖ ያገለግላል።  የመረጃ ባለሙያው ስለ PAIA ለሚነሱ ማንኛውም ጥያቄዎች መፍትሔ የመስጠት እንዲሁም የ POPIA አፈጻጸምን የመከታተል ኃላፊነት አለበት።  CCA የመረጃ ባለሙያ ለመቅጠር ወስኗል።  የመረጃ ባለሙያው አድራሻ እንደሚከተለው ነው፦

የመረጃ ባለሙያ

Mpumelelo Mazibuko (አቶ)

አድራሻ

Building 1, Oxford & Glenhove Road, Houghton Estate, 2198, Johannesburg

ስልክ ቁጥር

0860112526

የኢሜይል አድራሻ

dpoafrica@coca-cola.com5.  ያለ PAIA ጥያቄ የሚገኙ መረጃዎች[3]

5.1.  PAIA ለሁሉም ሰው የመረጃ ተደራሽነት ቀላል እንዲሆን ይጥራል።  ይህንንም የሚያስፈጽመው እንደ CCA ያሉ ድርጅቶች በራሳቸው ተነሳሽነት ሊጠየቁ የሚችሉ መረጃዎችን እንዲሁም መዝገቦችን ያለ PAIA ጥያቄና ሂደት እንዲያቀርቡ በመጠይቅ ነው።
[4]
5.2.  በ CCA ድረ ገጽ ላይ መረጃ ወዲያውኑ ይገኛል። ይህም የ PAIA ጥያቄ ሂደትን ሳይከተሉ መረጃን እንዲያገኙ ያግዛል።  በራሪ ወረቀቶቻችን፣ መግለጫዎቻችን፣ እትሞቻችን እና የማስታወቂያ ጽሁፎቻችን ወዲያውኑ ይገኛሉ።

6.  ከሌሎች ህጎች ጋር በተያያዘ የሚቀመጡ መዝገቦች[5]
6.1  ለተለያዩ ህግጋቶች እና ደንቦች ተገዢ ነን፣ ከእነዚህም ውስጥ አንድ አንዱ የተወሰነ መረጃን እንድናስቀምጥ ያስገድዱናል።  ተገዢ የሆንባቸውን እንዲሁም መዝገቦችን እንድናሰቅምጥ የሚያስገድዱንን ህጎች ከዚህ በታች አስቀምጠናል።

መሰረታዊ የስራ ደህንነት ህግ 75/1997
ጠቅላላ ጥቁር ማበረታቻ ህግ 53/2003 እና
የመልካም ድርጅታዊ አስተዳደር
ህግ 71/2008
በስራ ላይ ለሚከሰቱ አደጋዎች እና የጤና እክሎች ማካካሻ
ህግ 130/1993
የውድድር ህግ 89/1998
የቅጂ መብቶች ህግ 98/1978
የሸማቾች ጥበቃ ህግ 68/2008 የኤሌክትሮኒክ ኮምዩኒኬሽን ህግ 36/2005
ፍትሃዊ የስራ ቅጥር ህግ 55/1998
የፋይናንስ ደህንነት ማዕከል ህግ 38/2001
የገቢ ግብር ህግ 58/1962
የኪሳራ ህግ 24/1936
የአሰሪና ሰራተኛ ህግ 66/1995
ብሔራዊ የብድር ህግ 34/2005
የስራ ጤንነትና ደህንነት ህግ 85/199
የጡረታ ፈንድ ህግ 24/1956
POPIA
የክህሎት ማሻሻያ ህግ 97/1998
የክህሎት ማሻሻያ ጭማሪ ህግ 9/1999
የደረጃዎች ህግ 8/2008
የንግድ ምልክት ህግ ቁጥር 194/1993
ተጨማሪ እሴት ታክስ ህግ 89/1991
6.2.   በምንችለው አቅም አስፈላጊ የምንላቸውን ህጎች ዝርዝር ለማቅረብ ሞክረናል። ሆኖም ግን ከላይ የተዘረዘሩት ህጎች ሁሉንም ላያካትቱ ይችላሉ።  በ PAIA ከተጠቀሱት ህጎች ውጭ ጠያቂው የጠየቀውን እንዲያገኝ፡የሚፈቅድ አዲስ ወይም ነባር ህግ ከተገኘ፣ ዝርዝሩን እንደ አስፈላጊነቱ እናዘምነዋለን።  ከሌሎች ህጎች አንጻር ወይም ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ መረጃን የማግኘት መብት አለኝ ብለው የሚያምኑ ከሆነ፣ የትኛውን ህግ መሰረት እንዳደረጉ መጥቀስ ይኖርብዎታል። ይህም የመረጃ ባለሙያው በተሰጠው መረጃ መሰረት ጥያቄውን እንዲያስተናግድ ያግዘዋል።


7.  በምንይዛቸው መዝገቦች ዙሪያ ያሉ አርዕስቶች እና የመዝገቦች ምድብ መግለጫ[6]
7.1.  PAIA መዝገቦቻችንን ተደራሽ የምናደርግበት መንገድ ቀላል እንዲሆን ያስገድደናል።  ይህን ተፈጻሚ ለማድረግ ከታች የመዝገቦቻችን አንኳር አርዕስቶችን በምድብ ከፋፍለን አስቀምጠናል፦

አርዕስት

ምድብ

የድርጅቱ መዝገቦች

·                የፍቃድና ምዝገባ ሰነዶች፤

·                መመስረቻ ደንብ፤

·                የዳይሬክተሮች ቦርድ ቃለ ጉባኤ እና ጠቅላላ ጉባኤ፤

·                በጽሁፍ የጸደቁ ሰነዶች፤

·                ዳይሬክተሮች / ኦዲተሮች / የድርጅት ጸሀፊ ህዝብ ግንኙነት እና ሌሎች የተሾሙበት መዝገቦች፤

·                የአክሲዮን መዝገብ እና ሌሎች ህጋዊ መዝገቦች፤ እና

·                ሌሎች ህጋዊ መዛግብት።

የገንዘብ አያያዝ መዝገቦች እና የግብር መዝገቦች

·                ዓመታዊ የወጪ ገቢ ሰነድ፤

·                የግብር ተመላሽ፤

·                የአካውንቲንግ መዝገቦች፤

·                የባንክ መዝገቦች፤

·                የባንክ ወጪ ገቢ ሰነዶች፤

·                የተከፈሉ ቼኮች

·                ኤሌክትሮኒክ የባንክ መዝገቦች፤

·                የንብረት መዝገቦች፤

·                የኪራይ ውሎች፤

·                ደረሰኞች፤

·                የተከፋይ መዝገቦች፤

·                ከገቢ ግብር ጋር የተያያዘ ለሰራተኞች የሚሰጥ ሰነድ፤

·                በሰራተኞች ስም ለ"ሳርስ" ጉዳይ የተከፈሉ ወጪዎች መዝገብ፤

·                የተጨማሪ እሴት ታክስ መዝገቦች፤

·                የክህሎት ማሻሻያ ጭማሪዎች፤

·                UIF፤ እና

·                የሰራተኞች ካሳ።

የሰራተኞች መዝገቦች

·                የቅጥር ስምምነት ውሎች፤

·                የቅጥር ፖሊሲዎች እና አሰራሮች፤

·                 ፍትሃዊ ቅጥር እቅድ፤

·                የጡረታ ፈንድ መዝገቦች፤

·                የውስጣዊ ምዘናዎች እና የጥፋት እርምጃ ውሳኔ መዝገቦች፤

·                የደሞዝ መዝገቦች፤

·                የስነምግባር መመሪያ፤

·                የፍቃድ መዝገቦች፤

·               የስልጠና መዝገቦች እና መመሪያዎች፤

·                በሰው ሀብት ክፍል የሚሰጡ የግለሰብ መዝገቦች፣
·                ተያያዥ የጽሁፍ ልውውጦች።

የጤና፣ ደህንነት እና የዘላቂ ልማት መዝገቦች

 ·                የጤና እና ድህንነት መዝገቦች

·                የሕንጻዎች ግንባታ ፍቃድ

·                ለሕንጻዎች የእሳት አደጋ ጥንቃቄ ፍቃድ

የግዢ ክፍል መዝገቦች

·                አገልግሎትን እና ምርትን ለማቅረብ የተዘጋጀ ቋሚ የቅድመ ሁኔታዎች መዝገብ

·                የኮንትራክተር፣ ደንበኛ እና አቅራቢ ስምምነቶች/ውሎች

·                የአቅራቢዎች፣ ምርቶች፣ አገልግሎቶች እና አከፋፋዮች ዝርዝር

·                ፖሊሲዎች እና አሰራሮች

·                ፕሮፖዛል እና የጨረታ ሰነዶች፤

የኦፕሬሽን

መዝገቦች

·                የመቆጣጠሪያ ፍቃድ መዝገቦች

·                የአገልግሎት ውሎች

·                ጠቅላላ የጽሁፍ ውይይቶች

·                የመድሕን ሰነዶች

የማርኬቲንግ መዝገቦች

·                የማስታወቂያ መሳሪያዎች

·                የምርት መረጃ አስተዳደር

የስጋት ኦዲት መዝገቦች

·                ኦዲት ሪፖርቶች

·                የስጋት መቆጣጠሪያ እቅዶች

የመረጃ እና ቴክኖሎጂ መዝገቦች

·                የኮምፒውተር ወይም ተንቀሳቃሽ ስልክ አጠቃቀም ፖሊሲ

·                የአደጋ ጊዜ ማገገሚያ እቅዶች

·                የሃርድዌር ንብረት መዝጋቢዎች

የኮርፖሬት

ማሕበራዊ

ፕሮጀክቶች

(CSI) መዝገቦች

·                የፕሮጀክቶች ሲ.ኤስ.አይ መርሀግብር / ፈንድ የሚያገኙ ድርጅቶች መዝገብ

·                ፈንድ ካገኙ ድርጅቶች ጋር የተገባ ውል እና መዝገብ
8.  የ PAIA ጥያቄ እኛ ጋር እንዴት ማቅረብ እንደሚችሉ የሚገልጽ መረጃ[7]

8.1.  ለ CCA የ PAIA ጥያቄ ማቅረብ ቢፈልጉ፣ በአባሪው ላይ ከሚገኘው ቅፅ ሲ ወደ መንግስት ማሳወቂያ ቁጥር R.187 በዕለት 15 ፌብሯሪ 2002 ብለው ወይም ተመሳሳይ ቅፅ ላይ መጠየቅ ይችላሉ።  ለእርስዎ ይመች ዘንድ ቅፁን ከዚህ መመሪያ ጋር አያይዘናል። ቅፅ ሲ በአባሪ 1 ላይ ተያይዟል።
8.2.  መዝገቦችን ለማግኘት ለሚኖሮት ማንኛውም ጥያቄ የመረጃ ባለሙያውን በዚህ መመሪያ ላይ በተጠቀሰው አድራሻ ወይም ኢሜይል ማነጋገር አስፈላጊ ነው። ተገቢውን መረጃ ለእርስዎ መስጠት እንድንችል በጥያቄ ቅፁ ላይ ስለራስዎ እና ስለሚፈልጉት መዝገብ ዝርዝር ማብራሪያ መስጠት አስፈላጊ ነው።  መዝገቦቹን በምን ዓይነት መንገድ ለምሳሌ፦ በሃርድኮፒ ወይም በኤሌክትሮኒክ/ሶፍት ኮፒ ማግኘት እንደሚሹም ማመልከት ይኖርቦታል።  በጽሁፍ ከምንሰጥዎ ምላሽ በተጨማሪ በሌሎች መንገዶች (ለምሳሌ፦ በስልክ ወይም በኢሜይል) እርስዎን ማግኘት እንደሚቻል እባክዎን ያሳውቁን።  ሌላ አማራጭ ካለተጨማሪ አድራሻዎን ያሳውቁን።

8.3.  የትኛውን መብትዎን ለማከበር ወይም ለማስጠበቅ እንዳሰቡ መናገርዎ እንዲሁም የተጠየቀው መዝገብ መብትዎን ለማስከበርና ለመጠበቅ እንዴት እንዳስፈለግዎት ማብራሪያ መስጠትዎ አስፈላጊ ነው።

8.4.  ጥያቄውን እያቀረቡ ያሉት ለሌላ ሰው ከሆነ፣ ህጋዊ ውክልና ወይም ስልጣን እንዳልዎት የሚያሳይ ማስረጃ ማስገባት ይኖርቦታል።  ይህ ማስረጃ በቂ መሆኑን የሚወስነው የመረጃ ባለሙያው ይሆናል።

8.5.  የተዘጋጀውን መደበኛ ቅፅ (በዚህ መመሪያ በአባሪ 1 ላይ ይገኛል) የማይጠቀሙ ከሆነ፣ የአሰራር ሂደቱን ባለመከተል ጥያቄዎ ላይስተናገድ፣ ላይፈቀድ (በቂ መረጃ ካልቀረበ ወይም ሌላ ምክንያት) ወይም መልስ ሊዘገይ ይችላል።

8.6.  ተገቢውን ክፍያ መክፈል እንዳለብዎት ለማሳወቅ እንወዳለን።  ለጥያቄዎችና መዝገቦችን ለማግኘት ለሚነሱ ጥያቄው የተወሰኑ ዝርዝር የክፍያ መጠኖች (ጥያቄው ፍቃድ ካገኘ) በዚህ መመሪያ አባሪ 2 ተቀምጧል።

8.7.  መዝገቦችን የማግኘት ጥያቄዎ በግል ጉዳይ ካልሆነ፣ የክፍያ መጠኖቹን (እንደ አስፈላጊነቱ) ፍቃዱን ከማግኘትዎ በፊት እናሳውቅዎታለን። የጥያቄ ክፍያ እንዲከፍሉ በመጠየቃችን ለድርጅታችን ወይም ለፍርድ ቤት ውስጣዊ ቅሬታ ወይም ማመልከቻ ማስገባት ይችላሉ።

8.8.  በጥያቄዎ ውሳኔ ላይ ከደረስን በኋላ በአስፈላጊው ቅፅ እናሳውቅዎታለን።

8.9.  ማመልከቻዎ ተቀባይነት ካገኘ፣ ለሚኖረው የማባዣ፣ የመፈለጊያ እና የማዘጋጃ ስራዎች ክፍያ ይጠያቃሉ። እንዲሁም መዝገቦቹን በመፈለግ እና በማዘጋጀት ለሚጠፋው ተጨማሪ ሰዓትም ክፍያዎች ይኖራሉ።

8.10.  በ PAIA መሰረት ለሚመጡልን ማንኛውም ጥያቄዎች በአግባቡ መዝነን እንደምናስተናግድ እባክዎ ልብ ይበሉ።  ምንም እንኳን ይህንን መመሪያ ብናሳትምም እንዲሁም ስላሉን መረጃዎች ወይም መዝገቦች በተለያዩ አርዕስቶች እና ምድቦች ብንገልፅም፣ በ PAIA ጉዳይ ከሚነሱት በቀር መረጃዎችን ወይም መዝገቦቻችንን የማግኘት ምንም ዓይነት መብት የልዎትም።  ለእርስዎ የተከለከሉ መረጃዎች የሚያካትቱት የተፈጥሯዊ ሰው (ወይም የግለሰቦች) የሶስተኛ ወገን መረጃ፣ የሶስተኛ ወገን ንግድ መረጃ፣ የግለሰቦች ደህንነት ወይም የንብረቶች ጥበቃ፣ መረጃቸው እንዳይመረት ወይም እንዳይታተም የህግ ከለላ ያላቸው እና የግል ድርጅት ንግድ መረጃ እና የሶስተኛ ወገን እና የግል ድርጅት የጥናት እና ምርምር መረጃን ነው ።9.  POPIA ጋር ተያያዥ የሆነ መረጃ[8]
9.1.  መግቢያ
POPIA ለሚሰጡን የግል መረጃ አያያዝ፣ አጠቃቀም እና አጠባበቅን በተመለከተ መረጃ ለእርስዎን እንድንሰጥ ያስገድደናል።  አስፈላጊውን መረጃ ከታች እንደሚከተለው አስቀምጠናል።

9.2.  ከ POPIA ተያይዞ ለሚነሱ ጥያቄዎ የሚሆን መረጃ

9.2.1.  የእርስዎን ማንነት ካረጋገጥን በኋላ ያለምንም ክፍያ ስለ እርስዎ ግላዊ መረጃ እንደያዝን እና እንዳልያዝን መጠየቅ እንዲችሉ POPIA ያዛል።  ስለ እርስዎ የተቀመጠውን መዝገብ ወይም መረጃ መጠየቅ ይችላሉ። የእርስዎን መረጃ የተጠቀመ ወይም እየተጠቀመ ያለውን ሶስተኛ ወገን ማንነት መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።

9.2.2.  ከ POPIA ጋር ተያይዞ ለሚነሱ የግል መረጃ ተደራሽነት ጥያቄዎች በ PAIA ላይ መመስረት አለባቸው።[9] ይህ ሂደት ከላይ አንቀጽ 8 ላይ ተጠቅሷል።  አገልግሎቱን ከመስጠታችን በፊት የእርስዎን የግል መረጃ በሚሰጥበት ጊዜ የሚጠየቀውን ክፍያ መጠን በጽሁፍ እናሳውቅዎታለን።  የግል መረጃዎን ከመስጠታችን በፊት ክፍያውን በተወሰነ ወይም ሙሉ በሙሉ እንዲከፍሉ ልንጠይቅዎት እንችላለን።[10]


9.2.3.  ማስተካከያ የመጠየቅ መብት አሎት። እንደ ሁኔታውም በተገቢው ቅፅ[11] የግል መረጃዎ እንዲወገድ ወይም እንዲጠፋ የመጠየቅ መብት አልዎት። የግል መረጃዎ እንዲስተካከል፣ እንዲወገድ ወይም እንዲጠፋ ከፈለጉ፣ ለመረጃ ባለሙያው በዚህ መመሪያ በአባሪ 3 በተያያዘው የፖስታ፣ የአካል ወይም የኢሜይል አድራሻ ከላይ የተጠቀሰውን ቅጽ በመጠቀም መጠየቅ ይችላሉ።

9.2.4.  እንደ ሁኔታው ተገቢውን ቅፅ በመጠቀም የእርስዎን መረጃ ማቀናበር በተመለከተ ቅሬታ ማስገባት ይችላሉ[12]።  ቅሬታ ካልዎት በአባሪ 4 ላይ የተያያዘውን ቅፅ በመሙላት ለመረጃ ባለሙያው ከላይ በተቀመጡት[13] የፖስታ ወይም የአካል አድራሻ ወይም በኢሜል አድራሻ ማቅረብ ይኖርቦታል።

9.3.  የማቀናበር ዓላማ[14]

9.3.1.  POPIA እንደሚያዘው ከሆነ የግል መረጃ መቀናበር የሚችለው ለተወሰነ ዓላማ ብቻ እንደሆነ ነው።

9.3.2.  መረጃ የሚቀናበርበት ዓላማ ከእርስዎ የምንሰበስበው የግል መረጃ ዓይነት እንዲሁም እንደ ውሂብ ግለሰብ ከእርስዎ ጋር ከሚኖረን የመረጃ ነክ ግንኙነት ላይ ይወሰናል።  መረጃ የሚቀናበርበት ዓላማ በተለምዶ መረጃው በሚሰበሰብበት ወቅት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግልጽ የሚደረግ ነው።   እባክዎን ለተጨማሪ ማብራሪያ የ CCA ን ግላዊነት ፖሊሲ ይመልከቱ። በዚህ ማስፈንጠሪያ ይገኛል፦ https://www.coca-cola.co.za/privacy-policy

9.4.  የሚቀናበር የግል መረጃ[15]

ውሂቡ የሚመለከተው ሰው ምድብ

የግላዊ መረጃው ምድብ

ተፈጥሯዊ ሰዎች

ስሞች፤ አድራሻዎች፤ ቦታ እና የፖስታ አድራሻ፤ የትውልድ ዘመን፤ እድሜ፤ መታወቂያ ቁጥር፤ ግብር ነክ ምረጃዎች፤ ዜግነት፤ ጾታ፤ የባንክ መረጃ፤ የግል አስተሳሰብ እና አመለካከት፤ እና ድብቅ/ምስጢራዊ የደብዳቤ ልውውጦች።

የአገር ውስጥ ሰዎች / ድርጅቶች

የተወካዮች ስም፤ የድርጅቱ ስም፤ ቦታ እና የፖስታ አድራሻ እንዲሁም የመገኛ መረጃ፤ የፋይናንስ መረጃ፤ የመመዝገቢያ ቁጥር፤ መመስረቻ ሰነዶች፤ የግብር ነክ መረጃዎች፤ ህጋዊ ፈራሚዎች፤ ተጠቃሚዎች፤ ዋና ተጠቃሚ ባለቤቶች።

የውጭ ሰዎች / ተቋሞች


ስሞች፤ የመገኛ አድራሻዎች፤ ቦታ እና የፖስታ አድራሽ፤ የፋይናንስ መረጃ አድራሻዎች፤ የትውልድ ዘመን፤ ፓስፖርት ቁጥር፤ ግብር ነክ መረጃዎች፤ ዜግነት፤ ጾታ፤ ድብቅ/ምስጢራዊ የደብዳቤ ልውውጦች፤ የመመዝገቢያ ቁጥር፤ የመመስረቻ ሰነዶች፤ ህጋዊ ፈራሚዎች፤ ተጠቃሚዎች፤ ዋና ተጠቃሚ ባለቤቶች

አገልግሎት ሰጪዎች

የተወካዮች ስም፤ የድርጅቱ ስም፤ ቦታ እና የፖስታ አድራሻ እንዲሁም የመገኛ መረጃ፤ የፋይናንስ መረጃ፤ የመመዝገቢያ ቁጥር፤ መመስረቻ ሰነዶች፤ የግብር ነክ መረጃዎች፤ ህጋዊ ፈራሚዎች፤ ተጠቃሚዎች፤ ዋና ተጠቃሚ ባለቤቶች


አማካሪዎች

የተወካዮች ስም፤ የድርጅቱ ስም፤ ቦታ እና የፖስታ አድራሻ እንዲሁም የመገኛ መረጃ፤ የፋይናንስ መረጃ፤ የመመዝገቢያ ቁጥር፤ መመስረቻ ሰነዶች፣ የግብር ነክ መረጃዎች፤ ህጋዊ ፈራሚዎች፤ ተጠቃሚዎች፤ ዋና ተጠቃሚ ባለቤቶች


ሰራተኞች / ኃላፊዎች / የወደፊት ቅጥረኞች / ባለአክሲዮኖች / በጎ ፍቃደኞች / የሰራተኛው ቤተሰቦች / ጊዜያዊ ሰራተኞች

ጾታ፤ እርግዝና፤ የትዳር ሁኔታ፤ ዘር፤ እድሜ፤ ቋንቋ፤ የትምህርት ደረጃ፤ የፋይናንስት መረጃ፤ የቅጥር ታሪክ፤ የመታወቂያ ቁጥር፤ የቅርብ ዘመድ፤ የልጆች ስም፤ ጾታና እድሜ፤ የቦታና ፖስታ አድራሻ፤ የመገኛ መረጃ፤ አመለካከት፤ የወንጀለኝነት ባህሪ እና/ወይም የወንጀል መዝገብ፤ የጤና ሁኔታ፤ የውጭ የንግድ ፍላጎት፤ የጤንነት መረጃ፦

የድረ ገጽ የመጨረሻ ተጠቃሚዎች / የመተግበሪያ የመጨረሻ ተጠቃሚዎች

ስም፣ የኤሌክትሮኒክ መለያ መረጃ፦ IP አድራሻ፤ የይለፍ መረጃ፤ ኩኪስ፤ ኤሌክትሮኒክ መተርጎሚያ መረጃ፤ የተንቀሳቃሽ ስልክ መረጃ፤ የ GPS መረጃ።

9.5.  የግል መረጃን ማቀናበር በተመለከተ የተቀባዮች ምድብ[16]


9.5.1.  ከታች ለተጠቀሱት አካላቶች የግል መረጃዎችን ልንሰጥ እንችላለን፤

በኮካ ኮላ ድርጅት ውስጥ ያሉ መዋቅሮች፤
አመራሮች፤
ሰራተኞ፤
ጊዜያዊ ሰራተኞች፤ እና የንዑስ ኮንትራት ኦፕሬተሮች
9.5.2.  የሰበሰብነውን የግል መረጃ ለየትኛውም አገልግሎት አቅራቢዎቻችን፣ የንግድ አጋሮቻችን ወይም ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ለሚያስጠቅሙን (በሌሎች አገራት ተቀምጠው የክላውድ አገልግሎትን የሚሰጡትን ጨምሮ) ልናሳውቅ እንችላለን።

9.5.3.  የግል መረጃዎችን ለመንግስት ተቆጣጣሪዎች፣ ለመንግስት ባለስልጣናት ወይም ዕንባ ጠባቂ ወይም ለሌሎች ባለስልጣናት (የግብር ባለስልጣናትንም ጨምሮ) ልናሳውቅ እንችላለን።

9.5.4  በተቻለ መጠን ሌላኛው ወገን የግል መረጃን እና ምስጢራዊነትን መጠበቅ እንዲችል የጽሁፍ ስምምነት እናደርጋለን።  በህግ በተጠየቅን ጊዜ ወይም ህጋዊ መብታችንን በምንጠቀም ጊዜ የግል መረጃን ልናሳውቅ እንችላለን።

9.6  ስለ መረጃ ደህንነት እርምጃዎች ጠቅላላ ሀሳብ[17]

የግል መረጃ እንዳይጠፋ፣ እንዳይወድም ወይም ያላግባብ እንዳይወገድ እና በህገ ወጥ መንገድ ጥቅም ላይ እንዳይውል ወይም እንዳይቀናበር CCA ተገቢውን የቴክኒካል እና ድርጅታዊ እርምጃዎችን በመጠቀም የመከላከል ስራ ይሰራል።  እነዚህ እርምጃዎች የሚከተሉትን ያካትታል፡-

ፋይርዎል፤
የቫይረስ መከላከያ ሶፍትዌር እና የማሻሻያ ሂደቶች፤
በአካል የመረጃ ቁጥጥር፤
የሀርድዌር እና ሶፍትዌር አጠቃቀማችን ደህንነቱ የተጠበቀ ማድረግ የመረጃ እና ቴክሎኖሎጂ መሰረተልማታችን አንኳር ነው።
 

አባሪ 1

ቅፅ ሲ
የግል አካል መዝገብን የማግኘት ጥያቄ

(የመረጃ ተደራሽነት አዋጅ አንቀፅ 53(1)፣ 2000 (አዋጅ ቁጥር 2/2000)) [ደንብ 10]ሀ.  የግል አካል ዝርዝር

ስራ አስኪያጅ፡

 

ለ.  መረጃውን የጠየቀው ሰው ዝርዝር
(ሀ) መረጃውን የጠየቀው ግለሰብ ዝርዝር መረጃ ከታች መጠቀስ አለበት።

(ለ) በሪፐብሊኩ ውስጥ አድራሻ እና/ወይም ፋክስ ቁጥር መረጃው ወደሚላክበት መጠቀስ አለበት።

(ሐ) መረጃውን መጠየቅ የሚያስችል ማስረጃ (ካስፈለገ መያያዝ ይኖርበታል)
ሙሉ ስም እና
የአያት ስም.............................................................................

መታወቂያ ቁጥር፦

የፖስታ አድራሻ፦ .............................................................................................................
ስልክ ቁጥር፦ (.........) ..................................
የፋክስ ቁጥር፦ (..............).........................................
ኢሜል አድራሻ፦                     ..................................................................................................................
ጥያቄው የቀረበው በውክልና ከሆነ፣ ጥያቄው የተጠየቀበት አቅም፦
 

ሐ.  ጥያቄውን ያቀረበው ሰው ተወካይ ዝርዝር

ይህ ክፍል የሚሞላው ጥያቄው በውክልና የሚቀርብ ብቻ ከሆነ ነው።
ሙሉ ስም እና የአያት ስም፦     .....................................................................................................................

የመታወቂያ ቁጥር፦

 

መ.  የመዝገቡ ዝርዝር
(ሀ) ጥያቄው የቀረበበትን መዝገብ ሙሉ ዝርዝር ይስጡ። መዝገቡን ለማግኘት እንዲቀል ከተቻለ የመዝገብ ቁጥሩንም ይጥቀሱ።
(ለ) የተሰጠው ቦታ ለመዘርዘር በቂ ካልሆነ፤ እባክዎን ተጨማሪ ገጽ ተጠቅመው ከዚህ ቅፅ ጋር ያያይዙት። ጠያቂው እያንዳንዱን ገጽ መፈረም ይኖርበታል።

 

1. የመዝገቡ ዝርዝር ወይም ጠቃሚ ክፍሎች፦

..............................................................................................................................
2. የመዝገብ ቁጥር (ከታወቀ)፦
..................................................................................................................................

3. ተጨማሪ የመዝገብ ዝርዝር፦

...............................................................................................................................


ሠ.  ክፍያዎች

(ሀ) መዝገብ ለማግኘት የሚቀርብ ጥያቄ የሚስተናገደው የማመልከቻ ክፍያ ከተከፈለ በኋላ ብቻ ነው። ይህ የእርስዎን የግል መረጃ ለማግኘት የሚያቀርቡትን ጥያቄ አያካትትም።
(ለ) የማመልከቻ ክፍያ መጠን ምን ያህል እንደሆነ እናሳውቆታለን።

(ሐ) መዝገብን ለማግኘት ለሚቀርብ ጥያቄ ማመልከቻ ክፍያ መጠን የሚወሰነው የሚጠቀሙት ቅፅ እና ለመፈለግና ለማዘጋጀት የሚወስደው ጊዜ ይሆናል።

(መ) የማመልከቻ ክፍያ አይመለከተኝም ብለው ካመኑ እባክዎን ከታች ምክንያቱን ያስቀምጡ።

 

ክፍያ ላይከፍሉ የሚችሉበት ምክንያት፦

...........................................................................................................................አባሪ 2

ከ PAIA ጋር በተያያዘ ለሚቀርቡ የግል አካላት ክፍያዎች

1.  በ PAIA ደንብ 9(2)(ሐ) መሠረት የመመሪያውን ቅጂ በልሙጥ ወረቅት ገጽ ልክ ለማግኘት 1,10 ራንድ ያስከፍላል።


2.  በ PAIA ደንብ 11 (1) መሠረት የማባዣ ክፍያ እደሚከተለው ይሆናል፦


(ሀ) ለእያንዳንዱ ልሙጥ ወረቀት ገጽ ፎቶ ኮፒ ክፍያው 1,10 ራንድ ይሆናል።

(ለ) በኮምፒውተር ወይም በማንኛውም ኤሌክትሮኒክ ለሚደረግ የልሙጥ ወረቀት ቅጂ ክፍያው 0,75 ራንድ ይሆናል።

(ሐ) በኮምፒውተር ለሚነበቡ ቅጂዎች -

(1) ስቲፊ ዲስክ 7,50 ራንድ፤

(2) በኮምፓክት ዲስክ 70,00 ራንድ።

(መ) (1) በልሙጥ ወረቀት ገጽ ላይ የታተሙ ምስሎችን ለመገልበጥ 40,00 ራንድ፤

(2) የምስሎችን ቅጂ ለማግኘት 60,00 ራንድ።

(ሠ) (1) የድምጽ ቅጂን ወደ ልሙጥ ወረቀት ገጽ ለመገልበጥ


20,00 ራንድ፤

(2) የድምጽ ቅጂ ለማግኘት 30,00 ራንድ።

3. የግል ጥያቄ ሳያካትት ለሚቀርቡ ጥያቄዎች የተወሰነ ክፍያ መጠን፣


በ PAIA ደንብ 11(2) መሠረት ክፍያው 50,00 ራንድ ይሆናል።

4. በ PAIA ደንብ 11(3) መሠረት ጠያቂ ለማመልከቻ ክፍያ የሚጠየቀው


እንደሚከተለው ነው፦

(1) (ሀ) ለእያንዳንዱ ልሙጥ ወረቀት ገጽ ፎቶ ኮፒ ክፍያው 1,10 ራንድ ነው።

(ለ) በኮምፒውተር ወይም በማንኛውም ኤሌክትሮኒክ ለሚደረግ የልሙጥ ወረቀት ቅጂ ክፍያው 0,75 ራንድ ይሆናል።

(ሐ) በኮምፒውተር ለሚነበቡ ኮፒዎች -

(1) ስቲፊ ዲስክ 7,50 ራንድ፤

(2) በኮምፓክት ዲስክ 70,00 ራንድ።

(መ) (1) በልሙጥ ወረቀት ገጽ ላይ የታተሙ ምስሎችን ለመገልበጥ


40,00 ራንድ፤

(2) የምስሎችን ቅጂ ለማግኘት 60,00 ራንድ።

(ሠ) (1) የድምጽ ቅጂን ወደ ልሙጥ ወረቀት ገጽ ለመገልበጥ

20,00 ራንድ፤

(2) የድምጽ ቅጂ ለማግኘት 30,00 ራንድ።

(ረ) መዝገቡን ለመፈለግ፣ ለማሰናዳት እና ለማቅረብ ለሚወስደው ለእያንዳንዷ ሰዓት 30,00 ራንድ የሚከፈል ይሆናል።

(2) በ PAIA ክፍል 54(2) መሠረት የሚከተለው ተግባራዊ ይሆናል፦

(ሀ) ክፍያው ከመከናወኑ በፊት ስድስት ስዓታትን ወይም ከዚያም በላይ እንደሚወስድ፤ እና


(ለ) አመልካቹ የማመልከቻ ክፍያውን አንድ ሶስተኛ ተቀማጭ ያደርጋል።

(3) ቀሪው ክፍያ የሚከናወነው ለአመልካቹ የመዝገቡ ቅጂ በተዘጋጀ ጊዜ ይሆናል።

 

አባሪ 3
የግል መረጃን የማስተካከል ወይም የመሰረትዝ ጥያቄ ወይም በግል መረጃ ህግ 24(1) (2013) (አዋጅ ቁጥር 4/2013) መሠረት የግል መረጃን የማስወገድ ወይም የመሰረዝ ጥያቄ
የግል መረጃ ጥበቃ ጋር የተያያዙ ደንቦች 2018
[ደንብ 3]

ማስታወሻ፦

1.  ቃለ መሃላ ወይም ሌሎች የሰነድ ማስረጃዎች ከማመልከቻው ጋር መቅረብ ይችላሉ።

2.  በዚህ ቅፅ የተሰጠው ቦታ በቂ ካልሆነ ተጨማሪ ገጽ በመጠቀም፣ እያንዳንዱ ገጽ ላይ በመፈረም ከዚህ ቅፅ ጋር አባሪ ያድርጉት።

3.  እንደ አስፈላጊነቱ ይሙሉ።

ትክክለኛው ሳጥን ላይ "X" ምልክትን ያስቀምጡ።
የተጠየቀው፦

በአንድ አካል ባለቤትነት ወይም ቁጥጥር ስር የሚገኝን ስለ ውሂብ ግለሰቡ ያለ የግል መረጃ ለማስተካከል ወይም ለመሰረዝ።

መረጃውን የመያዝ መብቱ አብቅቶ ነገር ግን በአንድ አካል ባለቤትነት ወይም ቁጥጥር ስር የሚገኝን ስለ ውሂብ ግለሰቡ ያለ የግል መረጃ ለማስወገድ ወይም ለመሰረዝ።መረጃው የሚመለከተው አካል ዝርዝር

ስም (ስሞች) እና የአያት ስም /

መረጃው የተመዘገበበት ስም

ጉዳዩ፡

 
ልዩ አድራሻ/

መታወቂያ ቁጥር፦

 
የመኖሪያ፣ ፖስታ ወይም

የንግድ አድራሻ
ኮድ ( )

ስልክ ቁጥር (ቁጥሮች)፦

 
ፋክስ ቁጥር/ኢሜይል

አድራሻ፦

 


የሚመለከተው አካል ዝርዝር

ስም (ስሞች) እና የአያት ስም /

የተመዘገበበት ስም

የሚመለከተው አካል፦

 
የመኖሪያ አድራሻ፣ ፖስታ ወይም

የንግድ አድራሻ፦

 
 
 
ኮድ ( )

ስልክ ቁጥር (ቁጥሮች)፦

 
ፋክስ ቁጥር/ኢሜይል

አድራሻ፦

 


የሚስተካከለው/ የሚሰረዘው/ የሚወገደው መረጃ
መ.

ክፍል 24(1)(ሀ) መሠረት በማድረግ በሚመለከተው አካል ባለቤትነት ወይም ቁጥጥር ስር የሚገኝ የመረጃውን ዝርዝር በተመለከተ


መረጃው *የሚስተካከልበት ወይም የሚሰረዝበት ምክንያት፤ እና ወይም


ክፍል 24(1)(ለ)ን መሠረት በማድረግ መረጃውን የመያዝ መብቱ አብቅቶ ነገር ግን

በሚመለከተው አካል ባለቤትነት ወይም ቁጥጥር ስር የሚገኝ መረጃው


የሚወገድበት ወይም የሚሰረዝበት ምክንያት።

(እባክዎን ጥያቄውን ወይም ማመልከቻውን ያስገቡበት ምክንያት በዝርዝር ያስቀምጡ)የተፈረመበት ...................................... ቀን ................. 20...........

......................................................

መረጃው የሚመለከተው ሰው/ ተወካይ ፊርማአባሪ 4

የመረጃ ጥበቃ ህግ 2013 (ቁጥር 4/2013) ክፍል 11(3)ን መሠረት በማድረግ የግል መረጃ ማቀናበርን የመቃወም ሂደት

የግል መረጃ ጥበቃ ጋር የተያያዙ ደንቦች 2018


[ደንብ 2]

ማስታወሻ፦

1.  ቃለ መሃላ ወይም ሌሎች የሰነድ ማስረጃዎች ከማመልከቻው ጋር መቅረብ ይችላሉ።


2.  በዚህ ቅፅ የተሰጠው ቦታ በቂ ካልሆነ ተጨማሪ ገጽ በመጠቀም፣ እያንዳንዱ ገጽ ላይ በመፈረም ከዚህ ቅፅ ጋር አባሪ ያድርጉት።

3.  እንደ አስፈላጊነቱ ይሙሉ።መረጃው የሚመለከተው አካል ዝርዝር

ስም (ስሞች) እና የአያት ስም /

መረጃው የተመዘገበበት ስም

ጉዳዩ፦

 
ልዩ አድራሻ/

መታወቂያ ቁጥር፦

 
የመኖሪያ፣ ፖስታ ወይም

የንግድ አድራሻ
ኮድ ( )

ስልክ ቁጥር (ቁጥሮች)፦

 
ፋክስ ቁጥር/ኢሜይል

አድራሻ፦

 


የሚመለከተው አካል ዝርዝር

ስም (ስሞች) እና የአያት ስም /

የተመዘገበበት ስም

የሚመለከተው አካል፦

 
የመኖሪያ አድራሻ፣ ፖስታ ወይም

የንግድ አድራሻ፦

 
 
 
ኮድ ( )

ስልክ ቁጥር (ቁጥሮች)፦

 
ፋክስ ቁጥር/ኢሜይል

አድራሻ፦

 


ክፍል 11(1)(መ) እስከ (ረ)ን መሠረት በማድረግ የመቃወሚያ ምክንያቶች (እባክዎን ለመቃወሚያው ዝርዝር ምክንያቶችን ያስቀምጡ)የተፈረመበት ...................................... ቀን ................. 20...........

......................................................

መረጃው የሚመለከተው ሰው/ ተወካይ ፊርማ[1] በ PAIA ክፍል 51(1)(ሀ)

[2] በ PAIA ክፍል 51(1)(ለ)(1) በ POPIA ክፍል 110 በተሻሻለው መሠረት።

[3] በ PAIA ክፍል 51(1)(ለ)(2) በ POPIA ክፍል 110 እንደተሻሻለው መሠረት።

[4] ይህ በ PAIA ክፍል 52(2) ተጠቅሷል።

[5] በ PAIA ክፍል 51(1)(ለ)(2) በ POPIA ክፍል 110 በተሻሻለው መሠረት።

PAIA [7] በ PAIA ክፍል 51(1)(ለ)(4) በ POPIA ክፍል 110 እና በ PAIA ክፍል 53 በተሻሻለው መሠረት።

[8] በ PAIA ክፍል 51(1)(ሐ) በ POPIA ክፍል 110 በተሻሻለው መሠረት።
[9] የ POPIA ክፍል 25።

[10] የ POPIA ክፍል 23(3)(ሀ) እና (ለ)።

[11] የ POPIA ክፍል 23(2) እና 24።

[12] የ POPIA ክፍል 11(3)(ሀ)።

[13] ቅፅ 2 የግል መረጃ ጥበቃ ደንቦች ጋር በተያያዘ።

[14] በ PAIA ክፍል 51(1)(ሐ) በ POPIA ክፍል 110 በተሻሻለው መሠረት።

[15] በ PAIA ክፍል 51(1)(ሐ)(2) በ POPIA ክፍል 110 በተሻሻለው መሠረት። በዚህ ክፍል ስር የተጠቀሱት መረጃዎች ሰፋ ያለ የመረጃ ምድቦችን ያመላክታል። ይህ ዝርዝር በቂ አይደለም።

[16] በ PAIA ክፍል 51(1)(ሐ)(3) በ POPIA ክፍል 110 በተሻሻለው መሠረት።