ኮካ ኮላ በየጊዜው እየተሻሻለ ሙሉ በሙሉ የለስላሳ መጠጥ ድርጅት እየሆነ ያለበት ሁኔታ ላይ ነው፡፡

"ቋሚ የሆነው ለውጥ ብቻ ነው" የሚለው ብሂል እውነት ነዉ።

21-10-2022

2010ዎቹ የለውጥ እና የፈጠራ አስርት አመታት ነበሩ፤ እነዚህም እድገቶች የተመሩት በዲጂታል ለውጥ እና ግዙፍ የመረጃ ቋቶች የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ኢኮሜርስ፣ ማህበራዊ ሚዲያ እና ባዮቴክኖሎጂን በማፋጠናቸው ነው። ሸማቾች ከመቼውም ጊዜ በላይ ምርጫዎቻቸው ላይ በራስ መተማመን ማንጸባረቅ ስለጀመሩ እና ስለግልጽነት ያላቸው አቋምም እየበረታ በመምጣቱ ድርጅቶች ተጠያቂነት እንዲሰማቸው ጫና ማሳደር በመቻላቸዉ የግዢ ፍላጎቶችም እንዲሁ ተቀይረዋል። 

"ደንበኞቻችንን ማዳመጥ እንዲሁም ለውጥ ከልብ መቀበል የDNA እና የእድገት ስትራቴጂያችን መሰረታዊ አካል ነው። በዚህም ምክንያት ሙሉ በሙሉ የመጠጥ ድርጅት የመሆን ሂደት ላይ ነን፤ ይህም የደንበኞችን ፍላጎት እና የግዢ ባህል ለውጥ በመከተል እቅዶቻችንና አሰራሮቻችን ላይ ለውጥ እናመጣለን።" በማለት የኮካ ኮላ ድቡብ አፍሪካ ፍራንቻይዝ ምክትል ፕሬዚዳንት Phillipine Mtikitiki አብራርተዋል።

የመጀመሪያው የኮካ ኮላ ምርት በ 1886 በአትላንታ መሃል ከተማ ተሽጧል። በመጀመሪያው ዓመት በቀን ዘጠኝ መጠጥ ብቻ ነበር ያቀረበው። አሁን ከ 136 ዓመታት በኋላ ግን በዓለም ዙሪያ በተለያዩ ምድቦች ከ 200 በላይ ምርቶች አሉን እና መጠጦቻችን በየቀኑ በዓለም ዙሪያ ይጣጣማሉ። 

የተለያዩ ምርቶችን ፣ በአነስተኛ እሽግ ማቅረብ እና ለደንበኞች ግልጽ የንጥረ ነገር መረጃ መስጠት የኮካ ኮላ አንኳር የቢዝነስ መርሆች ውስጥ ይካተታሉ። ከዘርፉ የላቁና የተለያዩ መጠጦችን የማቅረብ ስራችንን እየቀጠልን ተጨማሪ ጥቅም የሚሰጡ ምርቶች ላይ እንሰራለን። እነዚህም ለስላሳ መጠጦች፣ ውሃዎች፣ ጁሶች፣ የስፖርት መጠጦች፣ ብና እና ቀላል አልኮል መጠጦች ያካትታል።

"ዘላቂ እድገትን እና ትርፋማነትን ለማምጣት ምርቶቻችንን ማብዛት ብቻ ሳይሆን በታለመና በእቅድ በተመራ መንግድ የማስፋፊያ ስራዎቻችንን እያከናወንን ነው።" በማለት Mtikitiki ትናገራለች። 

ኮካ ኮላ ቀዳሚ የጤና ተቋማትን ምክር በመቀበል የስኳር መጠንን ከካሎሪ የቀን አጠቃቀም 10% በታች እንዲሆን ተስማምቷል። በአሁኑ ሰዓት ከስኳር ነጻ እና አነስተኛ የስኳር መጠን ያላቸዉን ምርቶች በማቅረብ ላይ እንገኛለን። በደቡብ አፍሪካ ከ 2016 እስከ 2020 እ.ኤ.አ በስኳር የጣፈጡ መጠጦቻችን ላይ 32 በመቶ የስኳር መጠን ቅናሽ አድርገናል። 

የእሽጎቻችን መጠን ላይም እያሰብንበት ይገኛል፤ በፕሮግራሞች ላይ ለማካፈል እንዲመች ትላልቅ እሽጎችን እና አንድ ጊዜ ለመውሰድ ደግሞ አነስተኛ እሽጎቻችንን ለማቅረብ አስበናል። እያንዳዱ እሽግ ግልጽ የሆነ የንጥረ ነገር ይዘት መረጃ በመለጠፍ ደንበኞች ትክክለኛ የአመጋገብ ውሳኔ መወሰን እንዲችሉ እና መጠጦቻችንን በፈለጉት እሽግ መጠን ማጣጣም እንዲችሉ ያግዛል። ኮካ ኮላ ላይት እና ከስኳር ነጻ መጠጦቻችንን በማስተዋወቅ በአርአያነት እየመራን እንገኛለን።

እኛ አካባቢያዊ መሰረት ያለን ኩሩ ዓለም አቀፍ ድርጅት ነን። እ.ኤ.አ ከ 1928 ጀምሮ የደቡብ አፍሪካ ታሪካዊ ክስተቶችን ስናጋራ ቆይተናል። ለአገሪትዋ ኢኮኖሚ እድገት እንዲሁም ለአገር በቀል ቢዝነሶችም ድጋፍ ሆነናል። ጥራት ያላቸው አገር ውስጥ የተመረቱ ግብዓቶችን በመግዛት እንዲሁም ለአከፋፋዮቻችን የንግድ ክህሎት ስልጠና በመስጠት ድጋፍ በማድረግ በእሴት ሰንሰለታችን ውስጥ የስራ እድል የመፍጠር ሂደቱን እንቀጥላለን። 

ከመጠጥ አምራች አጋሮቻችን ጎን ለጎን በምንሰራባቻው አካባቢዎች ያሉ ማህበረሰቦች ላይ አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት ከመንግስት፣ ከአካባቢው ማህበረሰቦች፣ አጋር ኢንዱስትሪዎች እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር አብረን እንሰራለን። በተጨማሪም የኮካ ኮላ ስርዓት እና የመጠጥ አምራች አጋሮቻችን ከአካባቢዉ አቅራቢዎች እቃ እና አገልግሎት ግብይት በመፈጸም እንዲሁም በካፒታል ቁሶች ሽያጭ የአካባቢው ነዋሪዎችን ከታክስ ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል እና ከማህበራዊ ልማት ስራዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

Benjamin Franklin ብዙ ግዜ እንዳለው፣ "በህይወት ዉስጥ ቋሚ የሆነው ለውጥ ብቻ ነው። የአንድ ሰው ከለውጦቹ ጋር መላመድ መቻል የእርስዎን ስኬት ይወስናል።" ኮካ ኮላ ምርቶቹን ለለውጥ ዝግጁ ማድረጉን፣ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈውን ምርት ማሻሻሉን እና በደቡብ አፍሪካ እና በዓለም ደረጃ ዘላቂ ልማት ላይ የተኮረ ቢዝነስ መገንባቱን ይቀጥልበታል። ይህንን ሁሉ የምናደርገው፦ ዓለምን ለማደስ እና ለውጥ ለመፍጠር ካለንበት ዓላማ ጋር በመስማማት ነው።