የአገር ቅርስ የሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅት

በሴፕቴምበር 24 ታስቦ የሚውለው የቅርስ ቀን የአገራችንን የብዝሀነት እና የባህል ሀብት ይዘክራል እንዲሁም እዉቅና ይሰጣል።

24-09-2022

ይህ ቀን ምንም እንኳን በ 1996 እውቅና ቢሰጠውም የዚህ ቀን ታሪካዊ ዳራ በአገራችን ላይ ከፍተኛ ተጽኖ ሲያሳድር ቆይቷል። ኮካ ኮላ በታሪካዊ ትዉስታ ኃይል ላይ ጥልቅ የሆነ እምነት አለው። ድርጅቱ ደቡብ አፍሪካ የገባው በ 1928 እ.ኤ.አ ሲሆን እንደ ዓለም አቀፍ ድርጅት አገር በቀል አሻራ በማሳረፋችን ኩራት ይሰማናል። የተለያዩ ምርቶቻችን በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ተወዳጅነት አግኝተዋል እና በምንሰራባቸው አካባቢዎችና ማህበረሰቦች ላይ ቢዝነሳችን አዎንታዊ ተጽኖ በማሳረፍ ይገኛል።

ደቡብ አፍሪካ ያለ ምንም ጥርጥር ውብ አገር ናት፤ ተፍጥሮአዊ ሀብቶቿን መንከባከብ ከቅርስ ጥበቃ ስራዎች ውስጥ አንኳር ቦታውን ይይዛል። በመሆኑም ኮካ ኮላ በደቡብ አፍሪካ ዉስጥ በሁሉም የቀን ስራ ዘርፎቹ ውስጥ ዘላቂ ልማትን ቅድሚያ በመስጥ እየሰራ ይገኛል።

በ 2022 እ.ኤ.አ መጀመሪያዎቹ ላይ ኮካ ኮላ እና አጋሮቹ የኩባንያዉ የዘላቂ ልማት ስራዎችን ያዋቀረ JAMII የተሰኘ ስርዐት አስመርቀዋል። JAMII በቆሻሻ አያያዝ፣ የውሃ አስተዳደር እና የወጣቶች እና የሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ባሉ ሶስት ስትራቴጂካዊ መርሆች ያተኩራል። JAMII እነዚህን መልካም ተሞክሮዎች ወደ ፊት ለማስቀጠል ተመሳሳይ መርህ የሚከተሉ አጋሮችን መሳብ ይፈልጋል።

ውሃን መጠበቅ አገራዊ ግምባር ቀደም ዓላማ ነው እና ውሃ አዘል መሬቶችን ለመንከባከብ ሲባል ተንሰራፍተው የሚገኙ አረሞችን የማስወገድ ስራ በከፍተኛ ሲሰራ ቆይቷል። በ 2022 መጀመሪያዎቹ ላይ ኮካ ኮላ ፋውንዴሽን (TCCF) በአራት አዳዲስ ፕሮጀክቶች ሀብቱን በማፍሰስ በየዓመቱ በሚልዮን ሊትር የሚገመት ውሃ በመውሰድ የሚታወቁ መጤ ተክሎችን የማጽዳት ስራ እየሰራ ይገኛል። በ987,571 ዶላር እርዳታ የተጀመሩት እነዚህ ፕሮጀክቶች ውድ የሆነውን ውሃ ወደ ተፈጥሮ በመተካት ዘላቂ ልማትንና ታዳሽ ኢኮኖሚን ያፋጥናል።

ከዚህ ቀደም ከሪፕሌኒሽ አፍሪካ (RAIN) ጋር የተሰራው ስራ የሚበረታታ ውጤቶችን አስመዝግቧል። በደቡብ አፍሪካ በአምስት ፕሮጀክቶች ላይ 1,275 ሚልዮን ዶላር ወጪ በማውጣት 3,400 ሄክታር መሬት ላይ የሚገኙ መጤ ተክሎችን በማስወገድ ውሃን የመተካት ስራ ተሰርቷል። በተጨማሪ እነዚህ ፕሮጀክቶ ከ 100 የአካባቢ ትምህርት ቤቶች ጋር በመሆን ተማሪዎችን ስለውሃ ንጽህና እና ውሃ አጠባበቅ ትምህርት ሰጥተዋል።

በቅርስነት ተጠብቆ ያለውን "ሮቢን ደሴት" የመጠበቅ ኃላፊነታችንንም በተጨማሪም እየተወጣን እንገኛለን። የማጽዳት እና የመልሶ መጠቀም ሳምንትን በማስመልከት የኮካ ኮላ ፔኒንሱላ መጠጦች ሰራተኞችን እና የአካባቢው ነዋሪዎችን የያዘ የ 165 ሰዎች ስብስብ 750 ቆሻሻ ላሲኮችን በዚህኛዉ ሴፕቴምበር ወር ከሮበን ደሴት ዳርቻዎች ላይ አስወግዷል። በደቡብ አፍሪካ ኮካ ኮላ መጠጦች መሪነት በአገር አቀፍ ደረጃ በተካሄዱ ተመሳሳይ የጽዳት ዘመቻዎች በሺዎች የሚቆጠሩ የቆሻሻ ላስቲኮች ተሰብስበዋል።

የቆሻሻ አያያዝ የኮካ ኮላ ዘላቂ ልማት አጀንዳ ዉስጥ መሰረታዊ መርህ አካል ነው። "ዓለም ያለ ቆሻሻ" ፕሮጀክታችን መነሻ በማድረግ በእ.ኤ.አ 2030 ላይ በምናመርተው እያንዳንዱ ጠርሙስ ልክ እየሰበሰብንና መልሰን ጥቅም የማዋል እቅድ ይዘናል። የ PET ዳግመ ኡደት ድርጅት ከሆነው ከ PETCO ጋር በመተባበር እጅግ ብዙ የመሰብሰብ እና መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ፕሮጀክቶች ላይ እየሰራን እንገኛለን። በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከ63% በላይ የፕላስቲክ ድግመ ኡደት ስራዎችን ከ PETCO ጋር በመሆን እየደገፍን እንገኛለን። በ 2021 በተደረገው የድግመ ኡደት እና ለቀማ ስራ 90 402 ቶን የተጣሉ PET ተሰብስበዋል፤ በመሆኑም 560 495 ኩቢክ ሚትር የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ሊይዝ የሚችል ስፍራ ማትረፍ ተችሏል።

በአሁኑ ሰዓት አዲስ እና ግምባር ቀደም ፕሮጀክት እየሆነ ያለው የድግመ ኡደት ኢንደስትሪን ዲጂታል ማድረግ ነው። ከ TCCF ድጋፍ በማግኘት PETCO የ"ፕሮጀክት አፕ" ፕሮጀክት በመምራት ላይ ይገኛል። ይህም "BanQu" የተሰኘውን የብሎክቼን ቴክኖሎጂ የሚጠቀም ፕሮጀክት ነው። "BanQu" ዘመናዊ የመዝገብ አያያዝ ስርዓት ነው፤ እንዲሁም የድግመ ኡደት ቁሶችን ግብይትና ክትትል ያሳለጠ መሰሪያ ነው። በዚህም ምክንያት ደቡብ አፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ብሔራዊ የዳግመ ኡደት ዲጂታል መዝገብ እየገነባች ትገኛለች።

ኮካ ኮላ በደቡብ አፍሪካ አገር በቀል ግብዓቶችን ከመነሻው እየሸመተ እና አከፋፍዮችን በመደገፍ በእሴት ሰንሰለት ውስጥ የስራ እድሎች እያበረታታ ይገኛል። ከመጠጥ አምራች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የኮካ ኮላ ስርዓት በቀጥታ ለ 10,000 ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል። በተጨማሪም ይህ ስርዓት የአካባቢው ነዋሪዎችን በእቃ እና አገልግሎት ግብይት እንዲሁም በካፒታል ቁሶች ሽያጭ ከታክስ ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል እንዲሁም ከማህበራዊ ልማት ስራዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

በአካባቢው የሚገኙ ምርቶች የማደግ እድል እንዲያገኙ ኢንቨስት ማድረጋችንን እንቀጥላለን። እነ ስቶኒ፣ አፕልታይዘር እና ጋፕታይዘር የመሳሰሉ ምርቶች ከፍተኛ የሆነ የግብይት ኢንቨስትመንት እና የማከፋፈያ ድጋፍ ይደረግላቸዋል። በእነዚህ ድጋፎች የተነሳ ምርቶቹ በመላ ሀገሪቱ ዝናን እንዲሁም በየቤቱ ተዋዳጅነትን አትርፈዋል።

ዓለም አቀፍ ድርጅት ሆኖ በደቡብ አፍሪካ ታሪክ ያለው ኮካ ኮላ ደቡብ አፍሪካ ለ 94 ዓመታት ለደቡብ አፍሪካዊያን ደንበኞች እርካታን ሲያጎናጽፍ የቆየ እንደሆነ ሲያሳውቅ ከታላቅ ኩራት ጋር ነው።