#ጥዑምፋንታ በፋንታ™ በደቡብ አፍሪካ ቀረበላችሁ፡፡

ደንበኞችን የፋንታን አዲሱ ጣዕም ምን የምን እንደሆነ የሚጠይቅ አሳታፊ ፕሮግራም።

19-10-2022

ፋንታ™ በደቡብ አፍሪካ ዓለማቀፉን #ጥዑምፋንታ ፕሮግራም በይፋ አስመርቋል። ይህ ጣዕምን የመገመት ፕሮግራም የደንበኞችን የስሜት ህዋሳት በተለያዩ ጣዕሞች የሚፈትን ይሆናል፤ በድብቅ ስሙ ፋንታ™ ተብሎ የሚጠራው ውስን ምርት የዚህ ፕሮግራም አንኳር ሆኖ ይቀርባል። ፋንታ™ በፋንታ ዲጂታልና ማህበራዊ ገጽ ደንበኞቹ እንዲሳተፉና እንዲገምቱ እያበረታታ ይገኛል። ይህ ለየት ያለ ምርት በተለያዩና ለየት ባሉ ዘዴዎች ፍንጮችን ይሰጣል፤ መልሱም በኖቬምበር 1/2022 ይገለጻል።

በዚህ የመገመት ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ ደንበኞች #ጥዑምፋንታ እሽግን መግዛት ይኖርባቸዋል በመቀጠልም የዚህ ሚስጥራዊ ምርትን ጣዕም በመቅመስ ይሳተፋሉ። ስታዩት ታውቁታላችሁ- ቀለሙ ሰማያዊ ነው። መልስዎን ለመላክ በእሽጉ ላይ የሚታየውን QR ኮድ ስካን በማድረግ ከዛም ለዚህ ዐላማ በተዘጋጀዉ ወደ ፋንታ™ ድረ ገጽ በመሄድ መሳተፍ ይችላሉ። ጣዕሙን ለመለየት ተጨማሪ ፍንጭ ካስፈለግዎ ወደ ኢንስታግራም፣ ፌስቡክ እና የፋንታTM ማዕከል በማቅናት ሳምንታዊ ፍንጮችን ማግኘት ይችላሉ እና መልስዎ ትክክል ከሆነ አስገራሚ ሽልማቶችን የማግኘት እድል ይኖርዎታል። በኖቬምበር 1/2022 ሁሉም በፋንታ™ ዲጂታል እና ማህበራዊ ገጾች ላይ ይነገራል እና አሸናፊዎች ሚስጥሩን በማግኘታቸው ይፋ ይደረጋሉ።

በእዉነተኛ የፋንታ™ አሰራር ምልክቱ የግምታዊ ጨዋታውን እና አዝናኝን ወደ Mzansi የማህበራዊ ሚዲያ መጫወቻ ሜዳ፣ ኢንስታኔሽን በጆሃንስበርግ እያስፋፋ ነው። ፋንታ™ ለደንበኞች አሳታፊ እና አዲስ የሆነ - ኤግዚቢሽን ማስመረቅ ችሏል። እነ Khanyisa እና Alphi Sipho ን ጨምሮ ዝነኛ አርቲስቶች ተሳታፊ ሆኖዋል።

"ፋንታ™ ከልክ በላይ የተጨናነቀዉን ዐለም ወደተለያየ የጨዋታ መንፈስ ያሰገባል። ##ጥዑምፋንታ ጣዕም ከምርቶቻችን ውስጥ የጨዋታን መንፈስ የያዝ ብቸኛው ምርት ነው። በአንድ ጠርሙስ ውስጥ ጣዕምን የመገመት ጨዋታ ነዉ። የወጣት ደንበኞቻችን ዓለምን የማሰስ ፍላጎት፣ እምቅ ኃይል እና ጣዕምን የመለየት ጉጉት ወደዚህ እንድናመራ አነሳስቶናል።" ትላለች የደቡብ አፍሪካ ዋና የማርኬቲንግ ኃላፊ የሆነችው ክዋንዳ ድላሚኒ፡ ጣዕሞች።

#ጥዑምፋንታ ጣዕም በ 400 ሚሊ ሊትር እሽግ፣ 2.25 ሊትር PET፣ 2 ሊትር PET እና በ 440 ሚሊ ሊትር PET እሽጎች ለሽያጭ ቀርቧል።

ምዛንሲ (Mzansi) ምን ዓይነት አርኪ ጣዕም እንድሆነ ግምታቸውን ለመስማት በጉጉት በመጠበቅ ላይ ነን።


የመገናኛ ብዙሀን ገጾች እና ድረ ገጾች
ዩትዩብ
ፌስቡክ
ትዊተር
ፋንታ ሀብ